Jump to content

ዛዛኪኛ

ከውክፔዲያ

ዛዛኪኛ (Zazaki, Zazaish) በምስራቅ ቱርክ አገር በዛዛ ሕዝብ የሚናገር ቋንቋ ነው። የቱርክኛ ዘመድ ሳይሆን ከፋርስኛና ከኩርድኛ ጋር በሕንዳዊ-አውሮፓዊ ቋንቋዎች ቤተሠብና በሕንዳዊ-ኢራናዊ ንዑስ-ቤተሠብ ውስጥ ይገኛል። በተለይ የሚመስለው በስሜን ፋርስ አገር በካስፒያን ባሕር አጠገብ የሚገኘው ጊላኪኛ ነው።

የተናጋሪዎች ቁጥር ከ1.5 እስከ 2.5 ሚሊዮን እንደሚበዛ ይታመናል።

የዛዛኪኛ 3 ቀበሌኞች የሚናገሩበት ክልል

ሦስት ዋንኛ የዛዛኪኛ ቀበሌኞች አሉ:

  • ስሜን ዛዛኪኛ [1]
  • ማዕከለኛ ዛዛኪኛ
  • ደቡብ ዛዛኪኛ [2]

ሥነ ጽሑፍና ማሠራጫ በዛዛኪኛ

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

በዛዛኪኛ መጀመርያ የተጻፉት አረፍተ ነገሮች በ1842 ዓ.ም. በቋንቋ ሊቅ ፒተር ለርች የተከመቹ ነበር። ሌላ ሁለት ቁም ነገር ሰነድች አህማደ ሐሲ1891 ዓ.ም. እና ኡስማን ኤፌንዲዮ ባብጅ1925 ዓ.ም. የጻፉት ሃይማኖታዊ ጽሑፎች (ማውሊድ) በአረብኛ ፊደል ቀረቡ።

ዛዛኪኛ በላቲን አልፋቤት መጻፍ የጀመረበት ወቅት በ1970ዎቹስዊድንፈረንሳይና በጀርመን በተበተኑት ተናጋሪዎች በኩል ነበር። ከዚህ ተከትሎ አንዳንድ መጽሔትና መጽሐፍ በቱርክ አገርና በተለይ በኢስታንቡል ይታተም ጀመር። ከዚህ የተነሣ የዛዛ ወጣቶች ለእናት ቋንቋቸው አዲስ ትኩረት ይዘዋል። ከዚህ በላይ ቱርክ በአውሮፓ ኅብረት አባልነት ለማግኘት ስታስብ በሀገሩ በሚገኙ ትንንሽ ቋንቋዎች ላይ የነበሩትን ገደቦች አነሣችላቸው። ስለዚህ አሁን በቱርክ መንግሥት ማሰራጫ ድርጅት ላይ የዛዛኪኛ ቴሌቪዥንራዲዮ መደብ በየዓርቡ ተሰጥቷል።

ቃላት ከሌሎች ልሳናት ጋር ሲነጻጸር

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]
ዛዛኪኛ ኩርድኛ ፋርስኛ ቱርክኛ እንግሊዝኛ አማርኛ
አወ awe አቭ አብ su water ውሃ
አድር adır አጊር አታሽ od / ateş fire እሳት
አማየነ amaene ሃቲን አማዳን gelmek come መምጣት
አርደነ ardene አኒን አቫርዳን getirmek bring ማምጣት
አሽሚ aşmi ማንግ ማህ ay moon ጨረቃ
በርማዪሽ bermayış ጊሪን ገርየ ağlama cry ማልቀስ
ብራ bıra ቢራ ባራዳር kardeş brother ወንድም
በርዝ berz ቢሊንድ ቦላንድ yüksek high ከፍተኛ
በር ber ደር ዳር kapı door በር
ca ቺህ yer place ቦታ
ጀኒየ ceniye ዢን ዛን kadın woman ሴት
ጀዊያየነ cewiyaene ዢያን ዘንደጊ yaşamak live ሕይወት
ቺም çım ቻቭ ቸሽም göz eye ዓይን
ደስት dest ደስት ዳስት el hand እጅ
ደው dewe ደህ köy village መንደር
ኤርድ erd ኤርድ ዛሚን toprak earth ምድር
ኤስቶር estor አስፕ / አስታር አስብ / ኤስቲር at horse ፈረስ
ፈክ fek ደቭ ዳሃን ağız mouth አፍ
ግርድ / ፒል gırd / pil ጊር / መዚን ቦዞርግ büyük great ታላቅ
ጊሽት engışte/bêçıke አንጎሽት ኤንጉስት parmak finger ጣት
ሃክ hak ሄክ ቶሕም yumurta egg ዕንቁላል
ሄር her ከር ሓር eşek donkey አህያ
ሂረ hirê üç three ሦስት
ሆል hewl ባሽ ሑብ iyi good ጥሩ
ሆማ homa ሖዳ ሖዳ tanrı god አምላክ
ሁያየነ huyaene ከኒን ሐንደ gülmek laugh መሳቅ
ከርደነ kerdene ኪሪን ካርዳን yapmak make, do ማድረግ
ከየ keye ሐነ ሐነህ ev house ቤት
ከይ key ከንገ ከይ ne zaman when መቼ
ማየ mae ዳዪክ ማዳር anne mother እናት
ማሰ mase ማሂ ማሂ balık fish ዓሣ
መርደነ merdene ሚሪን ሞርዳን ölmek die መሞት
መርዲም merdım መር ማርድ erkek man ሰው
ናመ name ናቭ ናም ad / isim name ስም
ናን nan ናን ናን ekmek bread ዳቦ
pi ባቭ ፐዳር ata / baba father አባት
ቂጅ qıc ፒቹክ ኩቻክ küçük / ufak small ትንሽ
ራከርደነ rakerdene ቨኪሪን ባዝ ካርዳን açmak open መክፈት
ርንድ rındek ሪንድ ዚባ güzel beautiful ቆንጆ
ሮጅ roce ሮዥ ሩዝ gün day ቀን
ሰር ser ሰር ሳር kafa head ራስ
ሰረ serre ሳል ሳል sene year አመት
ሹንድ şan ኤቫር አሥር akşam evening ምሽት
ሸወ şewe ሸቭ ሻብ gece night ሌሊት
ሺያየነ şiyaene ቹን ራፍታን gitmek go መሔድ
ታርክ tari ታሪክ ታርክ karanlık dark ጨለማ
ተርስ ters ቲርስ ታርስ korku fear ፍርሃት
va ባድ rüzgar wind ንፋስ
ቫሽ vaş ቢሄሽ አላፍ ot grass ሣር
ቫተነ vatene ጊቲን ጎፍታን söylemek say ማለት
ቨርግ verg ጉር ጎርክ wolf ተኩላ
ቨይሻን veyşan ቢርችትዕ ጎሮስነጊ hungry ረሀብ
ቭዘር vızêr ዲሮውዝ ዱህ dün yesterday ትላንት
ዋየ wae ሕዊሽክ ሐሃር abla sister እህት
ዋስተነ waştene ሕወስትን ሐስታን istemek want መፈለግ
ወንደነ wendene ሕዋንዲን ሐንዳን okumak read ማንበብ
ወርደነ werdene ሕዋሪን ሖርዳን yemek food / eat ምግብ / መብላት
ወሽ weş ሕወሽ ሖሽ hoş / latif fine ደኅና
ዊን goni ሕውን ሑን kan blood ደም
ውሳር wesar ቢሃር ባሃር bahar spring ምንጭ
ዋሽተ waşti / waştiye ናም-ዛድ ደርጊስዕ sözlü / nişanlı fiancé ሙሽራ
ሖዝ xoz ሖክ ሑክ domuz pig ዓሣማ
ያ / ነ heya / nê ኤረ / ና አረ / ና evet / hayır yes / no አዎ / አይደለም
ዝዋን zıwan ዚማን ዛባን dil language ቋንቋ
ዘሪ zerri ዲል ደል yürek heart ልብ

The language differs from most Persian dialects in that it contains archaic strains of Hurrian; it has this in common with the languages Auramani (Hawrami or Gorani) and Bajelani, and these languages are put together in the Zaza-Gorani language group, but also Goran-Zazaistan by those who want emphasize their distinctness from the Kurds.

የዛዛኪኛ ጥናት

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ዋቢ መጻሕፍት

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]
  • Paul, Ladwig. (1998) The Position of Zazaki Among West Iranian languages. (Classification of Zazaki Language.)
  • Bozdağ, Cem and Üngör, Uğur. Zazas and Zazaki. (Zazaki Literature.)
  • Blau, Gurani et Zaza in R. Schmitt, ed., Compendium Linguarum Iranicarum, Wiesbaden, 1989, ISBN 3-88226-413-6, pp. 336-40 (About Daylamite origin of Zaza-Guranis)
  • Lezgîn, Roşan (2009) "Among Social Kurdish Groups – General Glance at Zazas", zazaki.net

የውጭ መያያዣዎች

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]
Wikipedia
Wikipedia