Jump to content

ሰኸምሬ ኹታዊ 1 ሶበክሆተፕ

ከውክፔዲያ

==

1 ሶበክሆተፕ
ምናልባት የሶበክሆተፕ ራስ ምስል፤ መታወቂያው እርግጥኛ አይደለም
ምናልባት የሶበክሆተፕ ራስ ምስል፤ መታወቂያው እርግጥኛ አይደለም
የግብጽ ፈርዖን
ግዛት 1819-1816 ዓክልበ.
ቀዳሚ ሶበክነፈሩ
ተከታይ ሰኸምካሬ ሶንበፍ
ሥርወ-መንግሥት 13ኛው ሥርወ መንግሥት
አባት 4 አመነምሃት?

==


ሰኸምሬ ኹታዊ 1 ሶበክሆተፕ ላይኛ ግብጽ2ኛው ጨለማ ዘመን (13ኛው ሥርወ መንግሥት) መጀመርያ ከ1819 እስከ 1816 ዓክልበ. ግድም ድረስ የገዛ ፈርዖን ነበረ። የንግሥት ሶበክነፈሩ ተከታይ ነበረ።

መቃብሩና ብዙ ቅርሶች በቅርቡ (2005 ዓ.ም.) ተገኝተዋል። የቶሪኖ ቀኖና በተባለው ፈርዖኖች ዝርዝር መሠረት በዚሁ ሥርወ መንግሥት በ19ኛው ሥፍራ ነገሠ፤ የግብጽ ታሪክ ሊቅ ኪም ራይሆልትሥነ ቅርስ ሰነዶች እንደሚያስረዳው ግን፣ በመጀመርያ ሥፍራ ከሶበክነፈሩ ቀጥሎ እንደ ነገሠ ይመስላል። አባቱ «አመነምሃት» ሲባል በራይሆልት አስተሳሰብ ይህ 4 አመነምሃት ሳይሆን አይቀርም። ስለዚህ ሶበክነፈሩ አክስቱ ትሆናለች።

በእርሱ ዘመን የ14ኛው ሥርወ መንግሥት መጀመርያ ፈርዖን ያክቢም ሰኻኤንሬአባይ ወንዝ አፍ ዙሪያ ለእርሱ ተገዥ ሆኖ ነገሠ። እነዚህ ከከነዓን የደረሱ ሴማዊ እረኞችና ነጋዴዎች ነበሩ። በጤቤስ ፈርዖኖች ፈቃድና ስምምነት ግዛታቸው በስሜን ግብጽ የንግድ ማዕከል ሆነ፤ ይህም በብሉይ ኪዳን ጌሤም የተባለው ሀገር ነው። ግብጽ እንደገና ተከፋፍሎ ይህ ወቅት የመካከለኛው መንግሥት መጨረሻ እና የ፪ኛው ጨለማ ዘመን መጀመርያ ይቆጠራል።

ቀዳሚው
ሶበክነፈሩ
ግብፅ (ጤቤስ) ፈርዖን ተከታይ
ሰኸምካሬ ሶንበፍ