4 አመነምሃት
Appearance
==
4 አመነምሃት | |
---|---|
የመዓትኸሩሬ እስፊንክስ ምስል | |
የግብጽ ፈርዖን | |
ግዛት | 1832-1823 ዓክልበ. |
ቀዳሚ | 3 አመነምሃት |
ተከታይ | ሶበክነፈሩ |
ሥርወ-መንግሥት | 12ኛው ሥርወ መንግሥት |
አባት | 3 አመነምሃት |
==
መዓትኸሩሬ፣ ፬ አመነምሃት ግብጽን በመካከለኛ መንግሥት (12ኛው ሥርወ መንግሥት) ከ1832 እስከ 1823 ዓክልበ. ግድም ድረስ የገዛ ፈርዖን ነበረ። የአባቱ 3 አመነምሃት ተከታይ ነበር።
በኒመዓትሬ 3 አመናምሃት ዘመነ መንግሥት መጨረሻ ዓመት ልጁን ፬ አመነምሃት ከእርሱ ጋር በጋርዮሽ ወደ ዙፋኑ አስነሣው።
የቶሪኖ ቀኖና በተባለው ፈርዖኖች ዝርዝር መሠረት መዓኸሩሬ ለ፱ ዓመታት፣ ፫ ወርና ፳፯ ቀን ነገሠ። በእርሱ ዘመን የማዕድን ጉዞ ወደ ሲና ልሳነ ምድር ከመላኩ በቀር ብዙ ድርጊት አልተፈጸመም። ምንም ልጅ እንዳልነበረው ይመስላል፤ ተከታዩ ሴት ፈርዖን ሶበክነፈሩ ስትሆን ይቺ እኅቱ እንደ ነበረች ይታመናል።
ቀዳሚው 3 አመነምሃት |
የግብፅ ፈርዖን | ተከታይ ሶበክነፈሩ |