መሲሊም
Appearance
መሲሊም ከሥነ ቅርስ የሚታወቅ የሱመር ንጉሥ ሲሆን ማዕረጉ «የኪሽ ንጉስ» ይባላል። ከኪሽ በላይ በአዳብና በላጋሽ ላይ ሥልጣን እንደ ያዘ ይመስላል፤ በነዚህም ከተሞች ቤተ መቅደሶች እንደ ሠራ ይዘገባል።
በእርሱ ዘመን ከላጋሽ ከንቲባ ሉጋል-ሻ-ኤንጉር እና ከተወዳዳሪው ከተማ ኡማ መካከል በጠረፋቸው ላይ ስለ ነበረው መስኖ አንድ ጠብ ተነሣ። መሲሊም ዕርቅና በመስጠቱ የሁለቱን ከተሞች ጠረፍ በዓምድ አስተካከለ። ሆኖም ከመሲሊም ዘመን በኋላ፣ የኡማ ንጉሥ ኡሽ ዓምዱን አፈረሰው።
በመምህሩ ኤድመንድ ጎርዶን (በ1950ዎቹ) አስተሳሰብ፣ ይህ መሲሊምና የኡር ንጉሥ መስ-አኔ-ፓዳ አንድ ንጉሥ ነበሩ። በዚያው ዘመን ያህል፣ የመስ-አኔ-ፓዳ መንግሥት እስከ ኡሩክ፣ ኒፑር፣ ኪሽና መላ ሱመር ድረስ ከተስፋፋ በኋላ እርሱ «የኪሽ ንጉሥ» የሚል ስያሜ ወሰደ። በተጨማሪ፣ አንድ ተረት በሱመርኛ፦ «መሲሊም ያሰራ የነበረውን የላጋሽ መቅደስ፣ ዘሩ የተቋረጠበት አናኔ አፈረሰው» ይላል። እንደ አጋጣሚ ግን አንድ የአካድኛ ተረት እንዲህ፦ «መስ-አኔ-ፓዳ ያሰራ የነበረውን መቅደስ፣ ዘሩ የተለቀመበት ናኔ አፈረሰው» ይላል። ስለዚህ ጎርዶን እንዳሰበው፣ የመሲሊምና የመስ-አኔ-ፓዳ ስሞች በዚህ ስለሚለዋወጡ፣ አንድ ንጉሥ ይሆናሉ።
- የመሲሊም ዱላ - ሥነ ቅርስ Archived ኦክቶበር 23, 2017 at the Wayback Machine