Jump to content

ኢላ-ካብካቡ

ከውክፔዲያ

ኢላ-ካብካቡአሦር ነገሥታት ዝርዝር ላይ በሁለት ሥፍራዎች የሚገኝ ስም ነው። በብዙ ምንጮች እነዚህ ግለሠቦች ተደናግረዋል።

መጀመርያው ኢላ-ካብካቡ «አባቶቻቸው የታወቁት 10 ነገሥታት» መካከል ይገኛል። ከአባቱ ያዝኩር-ኢሉ ቀጥሎና ከልጁ አሚኑ በፊት ይዘረዝራል። ይህም ምናልባት 2000 ዓክልበ. የሚያህል ዘመን ይሆናል።

ሁለተኛው ኢላ-ካብካቡ የአሞራዊ1 ሻምሺ-አዳድ አባት ነበር። ያው ኢላ-ካብካቡ የአሦር ንጉሥ ሳይሆን የተርቃ ንጉሥ በሶርያ ነበር። በማሪ ነጉሥ ያጊት-ሊም ወቅት እንደ ገዛ ይታወቃል።

«የማሪ ሊሙ ስሞች ዜና መዋዕል» የተባለው ሰነድ እንዳለው በ1746 ዓክልበ. «ኢላ-ካብካቡ ሱፕሩምን ያዘ።» በሚከተለው ዓመት ግን ልጁ «ሻምሺ-አዳድ ያባቱን ቤት ገባ»፣ ማለትም ንጉሥ ሆነ። ሻምሺ-አዳድ ከዚያ በኋላ ታላቅ ግዛት ለማሸንፍ በቃ፤ የአሦርም ንጉሥ ሆነና ሥርወ መንግሥት በዚያ መሠረተ።

በብዙ መምህሮች ግመት፣ «አባቶቻቸው የታወቁት ፲ ነገሥታት» በእውነቱ የሻምሺ-አዳድ ቀጥታ ዘር ሐረግ ነው፤ የአሦር ንጉሥነቱን ለማጽደቅ ወደ ዝርዝሩ እንደጨመረው ይሆናል ባዮች ናቸው። ይህን የሚያሥቡ ስሙ «ኢላ-ካብካቡ» በሁለቱ ሥፍራዎች ስለሚገኝ ነው። ዳሩ ግን አንድ ስም ያላቸው ልዩ ልዩ ሰዎች እንዳልሆኑ የሚያስረዳ ጽሑፍ የለም።