Jump to content

እምድብር

ከውክፔዲያ

እምድብርደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልልና የጉራጌ ዞን ከተማ ነው። የቸሃ ወረዳ መቀመጫ ነው።

እምድብር የመብራት ኃይል፣ የስልክና የፖስታ ቤት አገልግሎት ካሉዋቸው ከተሞች አንዱ ነው። የኢትዮጵያ ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን እምድብር ሀግረ ስብከት መሀል ነው።

ከ1924 ዓም ያሕል የካቶሊክ ካፑቺን መኖክሴ ሚስዮን እዚህ ተገኘ። የእምድብር ገበያ በየዓርቡ ይካሄድ ነበር።

የ1976 ዓም ድርቆት ዝናቡን ከልክሎ የእንሰት ሰብል በሙሉ በዚያው አመት በበሽታ ተበላሸ። የካቶሊክ እርዳታ አገልግሎት በልግሥናቸው ልብስ፣ በቆሎ፣ ወተት፣ ቅቤና ዘይት ለኗሪዎቹ አቀረቡ።

የሕዝብ ቁጥር በ1997 ዓም በ4057 ሰዎች ተቆጠረ።