ካሌብ
Appearance
ካሌብ በብሉይ ኪዳን ውስጥ የእስራኤል ሰው ነበረ። ከግብፅ ከጥልቅ ጭቆና ባርነት ከወጡ 603,550 ያህል ወንዶችና ቤተሠቦቻቸው ሁሉ[1] መካከል እርሱና ኢያሱ ወልደ ነዌ ብቻ ዮርዳኖስ ወንዝን በመሻገር ወደ ከነዓን በሕይወት እንዲገቡ ተፈቀዱ። ይህ የሆነው ኢያሱና ካሌብ በመንፈሳቸው ለእግዚአብሔር ስለ ታዘዙ ነው። ከግብጽ ያመለጡት ሌሎች ሁሉ በሲና ምድረ በዳ ዙሪያ ለ40 ዓመታት ቆይተው 601,730 ልጆቻቸው ወደ ከነዓን የዘመቱ ናቸው እንጂ ትውልዳቸው በሙሉ በ40 ዓመታት ውስጥ አልቀሩም።[2]
በፕሲውዶ-ፊሎ ዘንድ ወንድሙ ቄኔዝ ከኢያሱ ቀጥሎ የእስራኤል ፈራጅ ሆነ።
ጅምር! ይህ አጭር ጽሑፍ መሠረት ወይም መዋቅር ነው። አሁን ሊያስፋፉት ይችላሉ! |