ዋሻ ተፈጥሯዊ የሆነ እና በመሬት መቦርቦር የተፈጠረ ክፍተት ነው። ይህ ክፍተት ዋሻ ለመባል ቢያንስ ሰው የሚያስገባ መጠን ሊኖረው ይገባል። ሥነ-ዋሻ (Speleology) የሚባለው የሳይንስ ዘርፍ በዋነኛነት እንደ ዋሻ ያሉ ክፍተቶች እና አካባቢያቸውን ያጠናል።