አርሲ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች በከፍተኛ የደህንነት ስጋት ውስጥ መሆናቸውን ተናገሩ፡፡

[addtoany]

Sheger FM

በአሰላ የሚገኘው አርሲ ዩኒቨርስቲ ግብርና ካምፓስ የሚማሩ ተማሪዎች በከፍተኛ የደህንነት ስጋት ውስጥ መሆናቸውን ለሸገር ተናገሩ፡፡

ለሕይወታቸው በመስጋት ከዩኒቨርስቲው ቅጥር ጊቢ ወጥተው በጫካ ውስጥ ያደሩ መኖራቸውን ሰምተናል፡፡

በተለይ ከትናንት ጀምሮ በተማሪዎች መካከል በተፈጠረ አለመግባባት ተማሪዎች ወደ ግጭት መግባታቸውን ነግረውናል፡፡

በዚህም ምክንያት ለሕይወታቸው በመስጋት የዩኒቨርስቲውን ቅጥር ግቢ ለቅቀው ውጪ ማደራቸውን ለሸገር ተናገረዋል፡፡

ተማሪዎቹ ገጥሞናል ያሉትን ችግር በተመለከተ ሸገር የዩኒቨርስቲውን ፕሬዝዳንት ዱጉማ አዱኛን አነጋግሯቸዋል፡፡

ፕሬዝዳንቱ የፀጥታ ችግር መፈጠሩን፣ ችግሩንም ለመፍታት የፌደራልና የመከላከያ ሀይል አባላት ቦታው መድረሳቸውን ነግረውናል፡፡

ሙሉ ዘገባ ያዳምጡ